ከዲያቢሎስ ጋር የፈፀምነው ስምምነት ዋጋ እያስከፈለን ነው

ከዲያቢሎስ ጋር የፈፀምነው ስምምነት ዋጋ እያስከፈለን ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት Pius ፲፩ “አንድ መንግስት በማሕፀን ውስጥ ያለውን ህፃን ለመከላክል ካልቻለ፣ እግዚአብሔር ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮኸውን የንጹሐን ደም እንደሚበቀል አስታውሱ”። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ፍርሃት ይገልጻሉ፥ ፅንስ ማስወገድ የተለመደ ነገር እንዲሆን ስለተደረገ፣ ማኅበረሰባችን ከባድ ቅጣት ይደርስበታል።

ማኅበረሰባችን ቅጣት ይደርስበት ይሆን? እኔ የምመልሰው ይህ ነው፥ ዙሪያውን ተመልከቱ! ቀደም ብለው አለማችን የሚገባውን ቅጣት ተቀብሎአል፥ ዘርኝነት፣ የቤቶች መውደም፣ የቤተሰቦች ድህነት፣ ወንጀል፣ ባልና ሚስት መለያየት፣ ስራ አጥነት፣ የዕፅና የመጠት ሱስ። ወጣቶችም ስቃያቸው ለማሳየት ፀጉራቸው ቀይና ቢጫ ይቀባሉ።

በነዚህ ችግሮችና ፀንስን በማስወረድ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት ላይኖር ይችላል። የተቆጣም አምላክ እነዚህን ቅጣቶች በኛ ላይ እንዳደረሰ መጠቆም አልፈልግም። በእርግጥ የነዚህ ቅጣቶች ምክንያት ማኅበረሰባችን ራሱ ነው፥ ፅንስ ማስወረድን በመቀበሉ ከዲያቢሎስ ጋር ስምምነት ተፈራርሞአልና እነዚህ ችግሮች ሁሉም የስምምነቱ አካል ናቸው።

Leave a reply