የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ አውጥተዋል፥ የሰው ዘር ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ነው

የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ አውጥተዋል፥ የሰው ዘር ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ነው

ይህ አጀንዳ ዓለምን የሚያቅፍ አምባገነናዊ መንግሥት (New World Order) መጀመሪያው ይፋዊ አዋጅ ሊባል ይችላል። ይህ አዲስ አጀንዳ ሙሉ በሙሉ የሰው ዘር እንቅስቃሴዎችን ያካትታል።

በመጀመሪያ ሲታይ ይህ አጀንዳ እያንዳንዱን ከባድ ችግር በአለምአቀፍ ደረጃ ላይ የሚታገል ይመስላል። እስከ ዛሬ ድረስ ድህነትን ለማስወገድ በይፋ የሞከረ ሰው እንዳልኖረ ያስመስላል።

ይህ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል፥ ተሳታፊ ላለመሆን ለሚወስኑት አገሮች ምን ይሆናል? ድህነትን ከሚያስወግደው አለምአቀፋዊ እቅድ ነጻ ይሆናሉ ወይ?

በእነዚህ ዓለም አቀፋዊ ግቦች ላይ ለተመለከቱ ብዙዎቹ በጣም ጥሩ ይመስላሉ። ለመሆኑ ረሃብን ማቆም የማይፈልግስ ማን አለ?

ዋናው ቁም ነገር ከቋንቋው በስተጀርባ ያለውን ማየትና ምን እየተባለ እንዳለ መረዳት ነው። በእውነት እየተባለ ያለው ደግሞ ዓለምን የሚቆጣጠሩ ሀይሎች የአንድ ዓለም መንግሥት ሕልማቸውን ወደ ቀጣዩ ደረጃ መውሰድ እንደሚፈልጉ ነው።

2030 አጀንዳ ድብቅ ዓላማ

አላማ 1፥ ድህነትን በሁሉም ቦታ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት

ድብቅ ዓላማ፥ ሁሉም የዓለም ኢኮኖሚ በጥቂት መሪዎች ቁጥጥር ሥር ማድረግ፥ ማዕከላዊ ባንኮች ማቋቋም፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ (IMF)፣ የዓለም ባንክ ማቋቋም፣ ካሽ በሌለወ ማህበረሰብ ዓለምን በሚያቅፈው ዲጂታል ምንዛሬ መጠቀም።

አላማ 2፥ ረሃብን ማጥፋት፣ የምግብ ደህንነት መጠበቅ፣ የተሻሻለ አመጋገብ፣ ዘላቂ ግብርናን ማስፋፋት

ድብቅ ዓላማ፥ ዘሩ የተቀየረና የተዳቀለ ምግብ (እንዲህ አይነት ለሰው ጤና አደገኛ የሆነ ምግብ በእርዳታ ድርጅቶች በኩል በኢትዮጵያ ገጠሮች ለሕዝብ እየተሰራጨ ነው)።

አላማ 3፥ ጤናማ ህይወት ማረጋገጥ፣ በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች የጤና ደህንነትን ከፍ ማድረግ

ድብቅ ዓላማ፥ የሕዝብ ክትባት (ብዙ ክትባቶች ገዳይ መሆናቸውን ተረጋግጧል)፣ የተዳከመ ሰው መግደል (euthanasia)።

አላማ 4፥ ሁሉም አቀፍና ፍትሃዊ ጥራት ያለው ትምህርት መኖሩን ማረጋገጥ፣ የዕድሜ ልክ የትምህርት እድል ለሁሉም እንዲስፋፋ ማድረግ

ድብቅ ዓላማ፥ UN ፕሮፓጋንዳ፣ በአለም አቀፍ መሪዎች በሚመራ ትምህርት በኩል ከልደት እስከ ሞት ድረስ የሰውን አእምሮ መለወጥ ነው (አለም አቀፍ መሪዎች የአለም ፋይናንስ ተቆጣጣሪዎች ናቸው እንጂ የአገራት ፕሬሲዴንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች አይደሉም)።

አላማ 5፥ የፆታን እኩልነት ማረጋገጥ፣ ሁሉንም ሴቶች እና ልጃገረዶች ማበረታታት

ድብቅ ዓላማ፥ የወሊድና የሕዝብ ቁጥጥርን ማስገደድ።

አላማ 8፥ ሁሉም አቀፍና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማስፋፋት፣ ለሁሉም ሙሉ ውጤታማና   ተስማሚ የሆነ ሥራ ማስፋፋት

ድብቅ ዓላማ፥ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ­ጥቅም የሚደግፍ ነፃ የንግድ ቀጠናዎች ማቋቋም።

አላማ 11፥ ከተማዎችና የሰዎችን መኖርያ ሁሉን አቀፍ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው ማድረግ

ድብቅ ዓላማ፥ ሁሉን አቀፍ ግላዊ ዳታ የሚቆጣጠር መንግሥት(Big Brother)።

አላማ 12፥ ዘለቄታዊ ፍጆታና  መደበኛ ምርትን ማረጋገጥ

ድብቅ ዓላማ፥ አስገዳጅ የወጪ ቁጠባ መጠቀም (ሰው እንደፈለገ በራሱ ገንዘብ መጠቀም አይችልም ማለት ነው)።

አላማ 16፥ ዘላቂ ልማት እንዲኖር ሰላማዊና ሁሉን አቀፍ ማህበረሰብን ማበረታታት፣ ለሁሉም ፍትሕ መዳረሻ መስጠት፣ በሁሉም ደረጃ ውጤታማ ተጠያቂና  ሁሉን አቀፍ ተቋማትን መገንባት

ድብቅ ዓላማ፥ የUN “ሰላም አስከባሪ” ዘመቻ (የUN”ሰላም አስከባሪ” ዘመቻ ባለበት ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት አይጠፋም)፣ ዓይን የሌለው ዓለም አቀፋዊ ፍርድ ቤት ማቋቋም።

አላማ 17፥ ዘላቂ ልማት ተግባራዊ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ትብብር ማበረታታት

ድብቅ ዓላማ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመንግሥታትን ብሔራዊ ኃይል ማፍረስ፣ በተባበሩት መንግስታት ፖሊሳዊ አስተዳዳሪነትና ቢሮክራሲ ስር ዓለም አቀፋዊነትን (globalism) ማስፋፋት።

እስካሁን የጠቀስኳቸው ነጥቦች ሁሉ ለመረዳት ሊከብድ ይችላል። በአጭሩ ግን ከቁጥር 1 እስከ 17 ያሉት አላማዎች ምንድናቸው? ግለሰባዊና ማህበራዊ ነጻነትን የመቆጣጠርና የመገደብ መንገድ ናቸው። እነርሱን መቀበል ማለት ሁሉንም የህይወታችን ገፅታዎች የሚቆጣጠር መንግስትን መቀበል ማለት ነው። በእንግሊዝኛ ይህ ዓይነት መንግስት Big Brother ወይም New World Order ተብሎ ይጠራል።

ይህ አጄንዳ በመላው አለም አዲስ ሀይማኖትና አንድ አምልኮ እንዲኖር ይፈልጋል፥ የ2030 አጀንዳ የሁላችን አዲስ ሀይማኖት ሊሆን ማለት ነው?

Leave a reply