የሃይማኖት ብዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ (ሊቀ ጳጳሱ ፍራንሲስ)

የሃይማኖት ብዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ (ሊቀ ጳጳሱ ፍራንሲስ)

“የሃይማኖቶች የከለር የፆታ የዘር እና የቋንቋ ብዛት በእግዚኣብሄር ጥበብ የተፈቀደ ሁኔታ ነው”። ይህ መግለጫ ባለፈው የካቲት 4 በአቡ ዳቢ (ኤሚሬትስ) ፍራንሲስ እና የአል-አህዛር ታላቁ ኢማም በፈራረሙት ስምምነት ላይ የሚገኝ ነው።

በዘፍጥረት ምዕራፍ 11 የተጻፈው ግን እግዚአብሔር የቋንቋ መለያየትን እንደ ኃጢአት ቅጣት አድርጎ እንደፈቀደ ነው። ፍራንሲስ ሰዎችን እነደ መሥዋዕት የሚያርዱትን ሀይማኖቶች የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርገው ይቆጥሯቸዋል ማለት ነው። ስላሴንና የክርስቶስን መለኮትነት የሚቃረኑትን እስልምና ወይም ይሁዲነት የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርገው ይቆጥሯቸዋል።

እግዚአብሔር እርስ በራሳቸው የሚቃረኑትን ሃይማኖቶች ከፈቀደ፣ የፍራንሲስ አምላክ ሁለት ተቃራኒ አስተያየት ይደግፋል ማለት ነው። ልክ እንደ ሰይጣን እውነትንና የእውነት ተቃራኒ ይፈልጋል፥ በእርግጥ ሰይጣን የውሸት መርህ ነው።

ከኤሚሬትስ ሲመለሱ በበረራ ላይ በሚደረገው የጋዜጠኞች ጉባኤ ፍራንሲስ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፥ “ከካቶሊክ አመለካከት አንፃር የፈረምነው ስምምነት ከሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ አንድ ሚሊሜትር እንኳን አልተንቀሳቀሰም። ይህ ሰነድ የተፈረመ በሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ መንፈስ ነው”።

ነገር ግን ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ መንፈስ እና ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ጽሑፎች ሁለት የማይገናኙ ነገሮች ናቸው፥ የሌለ  የቫቲካን ጉባኤ መንፈስ እየተጠቀሰ ተገቢ ላልሆነ አካሄድ ክፍተት እየተሰጠ ነው (ሊቀ ጳጳሱ ቤኔዲክቶስ 22-12-2005 GC)።

Leave a reply